የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ነፃ አመታዊ የጤና ምርመራና ህክምና ማሰናዳቱ ተናገረ
TRACK

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ነፃ አመታዊ የጤና ምርመራና ህክምና ማሰናዳቱ ተናገረ

00:00

ሐምሌ 19፣ 2016

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ነፃ አመታዊ የጤና ምርመራና ህክምና ማሰናዳቱ ተናገረ፡፡

ሆስፒታሉ ከሀምሌ 19 እስከ 26 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ፣ ምክርና የህክምና አገልግሎት ማዘጋጀቱን ተናግሯል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ነዋይ ጸጋዬ አጠቃላይ ነፃ የህክምናና ምርመራ አገልግሎቶች ይሰጣሉ ብለዋል፡፡

ከነዚህም መካከል የካንሰር ቅድመ ምርመራዎች፣ የቆዳና አባላዘር፣ የህፃናት፣ የዓይን፣ አጠቃላይ ከአንገት በላይ ምርመራና ህክምናዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ለአገልግሎቱም በቂ ዝግጅት መደረጉን አቶ ነዋይ ነግረውናል፡፡

ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ነጣ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ተሰናድቶ እንደነበርና ከ45,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የተዘጋጀውን ነጣ አመታዊ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት ለማግኘት ካርድም ሆነ ሌላ መስፈርት አያስፈልግም የተባለ ሲሆን ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላል መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም

Comments

00:00