00:00
ነሐሴ 2፣2016
ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተጠለሉ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ ሁለቱ ክልሎች ስምምነት ላይ የመድረሳቸው ዜና ከሰማን ቆየን፡፡
ይሁንና አሁንም ወደነበሩበት የመመለሱ ስራ የዘገየ መሆኑን ሰምተናል፡፡
እንደማሳያ በደቡብ ወሎ ዞን ለዓመታት ከተጠለሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የተመለሱት 67 ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡
ለምን የተመላሾች ቁጥር አነሰ? የሌሎቹስ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል?
የዞኑ አደጋ ስጋት ፅ/ቤት አንጻራዊ ሰላም ወዳለበት የሚመለሱትን ለዩ በተባልነው መሰረት 8,400 የሚሆኑትን ብንለይም ከነዚውስጥ የተመለሱት 67ቱ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ በዞኑ 38,000 የሚሆኑ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments
00:00