ዩኒቨርሲቲዎች ከ4 ዓመት በፊት በተልዕኮና ትኩረት ተለይተው ይደራጃሉ ቢባልም ዛሬም ድረስ እውን አልሆነም
TRACK

ዩኒቨርሲቲዎች ከ4 ዓመት በፊት በተልዕኮና ትኩረት ተለይተው ይደራጃሉ ቢባልም ዛሬም ድረስ እውን አልሆነም

Avatar

ነሐሴ 28፣2016

ዩኒቨርሲቲዎች ከ4 ዓመት በፊት በተልዕኮና ትኩረት ተለይተው ይደራጃሉ ቢባልም ዛሬም ድረስ እውን አልሆነም፡፡

ለዚህ ደግሞ የትምህርት ሚኒስቴር ክትትል ማነስ እና የዩንቨርስቲ አመራሮች ለስራው የሰጡት ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርስቲዎችን በትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በምርምር፣ በአጠቃላይ ትምህርት እና የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በሚል በአምስት ዘርፍ ተከፍለዋል፡፡

ይህ ተልዕኮ በ2016 ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና(ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ በዚህ መንገድ ሳይዳጁ የቆዩበት ምክንያት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ለስራው የሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን፣ የትምህርት ሚኒስቴር ክትትል ደካማ መሆን ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ኤባ ከ51 ዩኒቨርሺቲዎች መካከል 4 ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮና ትኩረት ተደራጅተው በ2017 በጀት ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራሉ ይላሉ፡፡

እነዚህ ዩኒቨርስቲዎች የሰው ኃይል አደረጃጀታቸውና የትምህርት ፕሮግራሞቻቸው በተመደቡበትም መስክ አሰናድተው መጨረሳቸው ሰምተናል፡፡

Comments

Avatar