ተማሪዎች በሳይንስ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የትምህርት ዓይነቶች የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው ያግዛሉ የተባሉ አጋዥ መፅሀፍት ሊሰራጭ ነው
TRACK

ተማሪዎች በሳይንስ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የትምህርት ዓይነቶች የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው ያግዛሉ የተባሉ አጋዥ መፅሀፍት ሊሰራጭ ነው

Avatar

ነሐሴ 10፣2016

ተማሪዎች በሳይንስ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የትምህርት ዓይነቶች የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው ያግዛሉ የተባሉ አጋዥ መፅሀፍት በሀገር አቀፍ ደረጃ በትምህርት ቤቶች ሊሰራጭ ነው፡፡

እስከ አሁን በአዲስ አበባ አስር ትምህርት ቤቶች ላይ ተሰራጭቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አጋዥ የተባለው የዲጅታል መፅሀፍት ተማሪዎችን እንደጠቀማቸው ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ፣ የእንግሊዝ እና የህንድ ዜግነት ያላቸው ሶስት በጎ አድራጊ ሴት ተማሪዎች ባቋቋሙት GGE ወይም Girls Growing Education በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የኢትዮጵያ ተማሪዎችን በትምህርት ማብቃት እና ተወዳዳሪ ማድረግ ላይ እየሰራሁ ነው በሏል፡፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ ላሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ይደግፋል ያለውን አጋዥ መፅሀፍትን የያዘ መሳሪያ አምጥቶ መስራት ከጀመረ ሁለት አመታን አስቆጥሯል፡፡

ተማሪዎች ለሚማሩት መደበኛ ትምህርት ያግዛል የተባለለት ካለ ኢንተርኔት መስራቱ ደግሞ አጠቃቀሙን ቀላል ያደርገዋል የተባለ ሲሆን በአዲስ አበባ 10 በሚሆኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

በአሜሪካን ሀገር ፍቃድ አውጥቶ የሚሰራው የሄው ድርጅት ባሳለፍነው 2015 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አጠቃቀሙን በተመለከተ ለተማሪዎች የክረምት ስልጠና መስጠቱን ተናግሯል፡፡

Comments

Avatar