00:00
መስከረም 10፣2017
በኢትዮጵያ የፀረ ኤች አይቪ ኤድስ መድሃኒት ተጠቃሚዎች እና የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ተጠቂዎች የሚያገኙትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ፡፡
ስምምነቱን ያደረጉት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይቪ ኤድስ እርዳታ ፔፕፋር እና ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ናቸው፡፡
በአሜሪካ የፕሬዝዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይቪ ኤድስ እርዳታ ፔፕፋር ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከልና ተጠቂዎችን ለመርዳት የሚሆን 3 ቢሊየን ዶላር እርዳታ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፔፕፋር ኮሚቲኒ ሊድ ሞኒተር ፕሮግራም በሚል እየከወነው ያለው ስራ እራሱ ማህበረሰቡ ተሳታፊ ያደረገ ነው ምክንያቱ ደግሞ ቀጣይነት ያለው መሰረተ ልማት ለመገንባት ነው ብለዋል፡፡
Comments
00:00