TRACK
የብድር ጣሪያ በተወሰነ ፐርሰንት ከፍ ማድረግ እንዲቻል መንግስት ተወያይቶ አቅጣጫ የሰጠበት ጉዳይ መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታ ነግረውናል
ህዳር 17፣2017
14 በመቶ ላይ ብቻ የተቆለፈበት የብድር ጣሪያ በተወሰነ ፐርሰንት ከፍ ማድረግ እንዲቻል መንግስት ተወያይቶ አቅጣጫ የሰጠበት ጉዳይ መሆኑንን የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር ) ነግረውናል።
የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ጥብቅ የገንዘብ ማሻሻያ ፖሊሲዎችን ተግብሯል።
የሀገር ውስጥ ብድር እድገትም በ14 በመቶ ጣሪያ ተገድቧል።
በዚህ መሰረት ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሠረት እንዲያስተካክሉ ተነግሯቸው ቆይተዋል።
በዚህ ጉዳይና አጠቃላይ ለውጡ ምን ይመስላል ብለን የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታውን እዮብ ተካልኝን(ዶ/ር) ጠይቀናል።
እሳቸው ለውጡ የተሳካ እንደሆነ ተናግረዋል።
Comments