ሀገሪቱ  90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል እንዳላት ሲነገር ቢሰማም ለአብዛኛው ሰው ግን ስጋ ለዓመት በዓልም ቢሆን ብርቁ ነው
TRACK

ሀገሪቱ 90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል እንዳላት ሲነገር ቢሰማም ለአብዛኛው ሰው ግን ስጋ ለዓመት በዓልም ቢሆን ብርቁ ነው

Avatar

መጋቢት 26፣2016

ኢትዮጵያ የህዝቧን ቁጥር ሊስተካከል የተቃረበ ያህል በግ እና ፍየል እንዳላት ይነገራል፡፡

ሀገሪቱ 90 ሚሊዮን በግ እና ፍየል እንዳላት ሲነገር ቢሰማም ለአብዛኛው ሰው ግን ስጋ ለዓመት በዓልም ቢሆን ብርቁ ነው፡፡

ዋጋውም የሚቀመስ አልሆነም፡፡

የኢትዮጵያ በግ እና ፍየሎች በየድንበሩ እየተነዱ የኮንትሮባንድ ሲሳይ መሆናቸውም አልቀረም፡፡

የበግ እና ፍየል ስጋ ብርቅ እንዳይሆን በማሰብ የተለያዩ ሀገር ዝርያዎችን ወደ ሀገር ቤት በማምጣት፣ ለማዳቀል የተደረገው ጥረትም እንደታሰበው አልሆነም፡፡

የበግ እና ፍየል ስጋ ብርቅ እንዳይሆን፣ ተሽጠውም ዶላር እንዳያመጡ፣ እርባታውም አካባቢን እንዳይጎዳ ለማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ባለፉት 15 ዓመታት ሲሞከር መቆየቱን ሰምተናል፡፡

ፕሮግራሙ ''ማህበረሰብ አቀፍ የዝርያ ማሻሻያ'' እንደሚባል ሰምተናል፡፡

ከሌላ ሀገር ዝርያ ማምጣት ሳያስፈልግ እዚሁ ሀገር ቤት ካሉት የተሻሉትን ዝርያዎች በማዳቀል የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ተነግሯል፡፡

ፕሮጄክቱ በ 200 መንደሮች ተግባራዊ ተደርጎ ውጤቱም ጥሩ መሆኑን በአለም አቀፉ ድርቃማ አካባቢዎች የግብርና ምርምር (Icarda) ውስጥ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የግብርና_ምርምር #የእንሰሳት_ሀብት #በግ #ፍየል

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comments

Avatar