የላንሴት ሆስፒታል ሰራተኞች በደም እጦት ምክንያት ታካሚዎች እንዳይጎዱ በገና በዓል ዋዜማ  ደም ሲለግሱ ውለዋል
TRACK

የላንሴት ሆስፒታል ሰራተኞች በደም እጦት ምክንያት ታካሚዎች እንዳይጎዱ በገና በዓል ዋዜማ ደም ሲለግሱ ውለዋል

Avatar

ታህሳስ 29፣2016

በኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች የጋራ ባለሃብትነት የተቋቋመው የላንሴት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል ሰራተኞች በገና በዓል ዋዜማ ደም ሲለግሱ ውላዋል።

ሆስፒታሉ ባለፉት 3 ዓመታት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

አርብ ዕለትም የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች በደም እጦት ምክንያት እናቶች፣ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች እና ሌሎች ደም የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች እንዳይጎዱ ደም ሲለግሱ ውለዋል፡፡

ከለጋሾች የሚገኝ ደም በሚያንስባቸው ጊዜያት ቀዶ ህክምና የሚፈልጉ የህክምና አገልግሎቶች በደም እጥረት ምክንያት የቀጠሮ ጊዜያቸው እንደሚራዘም ሲነገር ይሰማል።

ለዚህም የላንሴት ሰራተኞች ደም እንለግስ ሲሉም ጥሪ አቅረበዋል፡፡

በረከት አካሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ላንሴት_አጠቃላይ_ሆስፒታል #የደም_ልገሳ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar