''ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የመቆረጥ ስጋት አለበት''  የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት
TRACK

''ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የመቆረጥ ስጋት አለበት'' የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

00:00

የካቲት 28 2017

ከጅቡቲ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ መተሃራ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የመቆረጥ ስጋት አለበት ሲል የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡

ስለዚህም ተለዋጭ መንገዶች እንዲሰሩ ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን አስረድቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውሷል፡፡

አሁን እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየጨመረ መጥቶ ድንገት ቢፈነዳ የገቢና ወጪ ንግድ የሚያልፍበት የኢትዮ ጅቡቲ ዋናው መንገድ መተሃራ አካባቢ የመቆረጥ ስጋት አለበት ብሏል፡፡

በስፔስ ሳይንና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ናትናኤል አገኘሁ እንዳሉት ፈንታሌ አካባቢ ቅላጭ ድንጋይ ወይም ማግማ ባለፉት 3 ወራት ወደ መሬት እጅጉን እየቀረበ መጥቷል ብለዋል፡፡

Comments

00:00