00:00
ዛላንበሳ ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ የኢሮብ አካባቢዎች ነዋሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ተናገረ፡፡
በዛላንበሳን ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት እጅ በሆኑ የኢሮብ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ ጽሕፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡
የፌደራል መንግስት እና በሃወሃት መካከል ተደርጎ በነበረው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ሰራዊት እጅ የገቡ አካባቢዎች ባለመለቀቃቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ ችግር እየደረሳባቸው እንዳለ የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ ፀሃዬ እንባዬ ነግረውናል፡፡
Comments
00:00