TRACK
''በትግራይ ክልል ባሉ ከተሞች ከቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል “የትኛውን ከንቲባ“ ተብዬ እየጠየቃለሁ'' የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም
00:00
ታህሳስ 21፣2017
ከቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል “የትኛውን ከንቲባ“ ተብዬ እየጠየቃለሁ ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡
በሕወሃት ፓርቲ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት ህዝቡ እየተንገላታ ነው ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡
በሕወሃት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከተሞች ሁለት ከንቲባ እና አስተዳደሪ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡
ይህም ተገልጋዩ ለእንግልት ዳርጓል ብሏል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፡፡
የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና አዲግራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉ አንዳንድ ወረዳዎች በጊዜአዊ አስተዳደሩም እና በእነ ደብረ ጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመራው ህወሃትም ከንቲባ እና አስተዳዳሪ ይሾምላቸዋል ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ አንባዬ አስታውሰዋል፡፡
Comments
00:00