የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ቢደርስም ለዓመታት እልባት ሳያገኝ የቀጠለ ጉዳይ ሆኗል፡፡
TRACK

የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ቢደርስም ለዓመታት እልባት ሳያገኝ የቀጠለ ጉዳይ ሆኗል፡፡

Avatar

ሚያዝያ 2 2017

“መምህራን እየተራቡ የትምህርትን ጥራት ማረጋገጥ አይቻልም” መምህራን

“የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ትምህርትን ለማሻሻል በጣም ወሳኝ ነው” የትምህርት ሚኒስቴር

ትውልድ ፊደል ቆጥሮ ከህልሙ እንዲደርስ መንገድ ጠራጊው፣ አቅጣጫ ጠቋሚው መምህር ለሞያው የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ ለማስተማር ፍላጎት እንዲጣ ምክንያት እንደሆነ ጥናት አሳይቷል፡፡

በደባርቅ ዩኒቭርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ፈለቀ ወርቁ “የዩኒቭርሲቲ መምህራን ሀገር እንድትቀጥል የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረው ይህን ማድረግ የሚችሉት ግን ሳይርባቸው ማስተማር ሲችሉ ነው” ብለዋል፡፡

“የዩኒቭርሲቲ መምህራን እየተራቡ ሀገርን አያስቡም ያሉት መምህሩ አሁን ለመምህራን እየተከፈለ ያለው ክፍያ ከአንድ የባንክ ቤት የጥበቃ ሰራተኛ ያነሰ ነው” ሲሉ ነግረውናል፡፡

Comments

Avatar