ህዳር 3፣ 2017
‘’በትጥቅ አመጽ ይንቀሳቀሱ ከነበሩት ጋር ስምምነት ፈጥሬ በጋራ እየሰራን ነው’’ ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡
ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎችን በካቢኒ አባልነትን ጨምሮ በተለያዩ የስራ መስኮች በመሳተፍ እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በክልሉ በአሁን ሰዓት ምንም አይነት የሚያሰጋ የጸጥታ ችግር የለም ሲል ክልሉ ለሸገር ራዲዮ ነግሯል፡፡
መንግስትን በመቃወም ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የተለያዩ ቡድኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ትጥቅ ፈትተዋል ተብሏል፡፡
ይህንን ለሸገር የነገሩት፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ የሰላም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ጸሀይ ጉዮ ናቸው፡፡
በክልል ቀድሞ የነበረው የጸጥታ ችግር ጥሎት ያለፈው ክፍተቶችን ለማስተካከል እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ይሁንን ወደ ሰላም የተመሱት ለመደገፍ ክልሉ የፋይናንስ እጥረት እንደገጠመው አቶ ጸሀይ ጠቅሰዋል፡፡
ይህንን ክፍተት ለማስተካከልም አየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments