TRACK
በጋሞ አካባቢ ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ዋናው ምክንያት ለአፈር ዓይነቱ የሚሆን የአካባቢ ጥበቃ ስራ ባለመስራቱ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አመነ
ነሐሴ 8፣2016
በጋሞ አካባቢ ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ዋናው ምክንያት ለአፈር ዓይነቱ የሚሆን የአካባቢ ጥበቃ ስራ ባለመስራቱ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አመነ፡፡
ጋሞን ጨምሮ በቅርቡ የመሬት መንሸራተት አደጋ የተከሰተባቸው የደቡብ አካባቢዎች የመሬት አቀማመጣቸው ተራራማ፤የአፈራቸው ዓይነት ደግሞ በባህሪው ብዙ ውሃ ይዞ የሚቆይ ሸክላማ አፈር መሆኑን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡
በየዓመቱ እስከ 2ሺህ ሚሊ ሚትር የሚደርስ ከባድ ዝናብ የሚዘንብበትም ነው፤ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል ለአካባቢው የሚያስፈልገው ከድንጋይ የሚሰራ እርከን ሆኖ ሳለ ያለው የአፈር እርከን በመሆኑ አፈሩ የበለጠ ውሃ እንዲይዝና አደጋው እንዲባባስ አድርጎታል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
Comments