TRACK
‘’በኢትዮጵያ ቢዝነስን ከማግዝ ይልቅ ቁጥጥርን ያስቀደሙ አሰራሮች መንገዱን አክብደውታል’’
ታህሳስ 19፣2017
ኢትዮጵያ ቢዝነስን አቀላጥፎ ለመስራት (Ease oF Doing Business) የማትመች፣ ጥልፍልፍ አሰራሮች ያሉባት መሆኑ ያለችባት ደረጃ ያሳያል፡፡
የአለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ቢዝነስን አቀላጥፎ ለማከናወን በሚያስችሉ አለም አቀፍ መመዘኛዎች ከ190 ሀገራት ደረጃዎች 159ኛ ላይ ነው፡፡
በጥንታዊነቷ፣ ንግድንም ቀድሞ በመጀመር፣ መገበያያንም በማኖር ቀድሞ ስሟ የሚጠቀሰው ኢትዮጵያ ስራ (ቢዝነስ) ለመስራት ያላት አመቺነት ግን ዝቅተኛ ወይም ከአለም ሀገር ከ31 ብቻ የተሻለ ነው፡፡
ለአብነትም በኢትዮጵያ የንግድ ምዝገባ ለማከናወን 32 ቀናትና 11 መስፈርቶችን ማሟላት ይጠይቃል ይላል የአለም ባንክ ሪፖርት፡፡
በኢትዮጵያ በግልም ይሁን ከሌሎች ጋር ሆኖ ሀሳብን አዋጥቶ ገንዘብ መስሪያ ቦታ ፈልጎ ስራ ሰርቶ ትርፋማ ለመሆኑ አድካሚ መንገዶችን መጓዝ ይጠይቃል፡፡
የበዛ የህዝብ ቁጥር፣ ስራ አጥ በበዛበት ሀገር፣ ስራ መስሪያው መንገድ ግን ለምን በመርፌ ቀዳዳ የማለፍን ጥበብ የሚጠይቅ ሆነ?
Comments