ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ እንዲሆን የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
TRACK

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ እንዲሆን የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ

Avatar

መስከረም 4፣2017

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር የህብረተሰቡን ችግር ፈቺ እንዲሆን የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰሩ የጥናት ምርምሮች የመደርደሪያ ጌጥ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የላቸውም በሚል በተደጋጋሚ ትችት ሲቀርብ ይሰማል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምር እና ስርፀት ዴስክ ኃላፊው ሰራዊት ሀንዲሶ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩት ጥናትና ምርምር የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ አይደለም ይላሉ፡፡

ችግሩ በተደጋጋሚ በጥናትና ምርምር ተረጋግጧል የሚሉት ኃላፊው ከሀገራዊ እና ተቋማዊ ጉዳዮች ጋር የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ቢተሳሰሩ አሁን የሚታየው ክፍተት መሙላት ይቻላል ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

Comments

Avatar