የጤና ሚኒስቴር የህክምና ተቋማት የሚሰጧቸውን የተለያዩ የህክምና አይነቶች ያካተተ መተግበሪያ አስመርቋል፡፡
TRACK

የጤና ሚኒስቴር የህክምና ተቋማት የሚሰጧቸውን የተለያዩ የህክምና አይነቶች ያካተተ መተግበሪያ አስመርቋል፡፡

Avatar

ህዳር 2 2018

በሀኪም የታዘዙ መድሀኒቶችን በቀላሉ ፈልጎ ማግኘት ብዙ ጊዜ ለተጠቃሚዎች ፈታኝ ይሆናል፤ አንዳንዶቹ መድሃኒቶች በተወሰኑ የመድኃኒት መደብሮች ወይም ፋርማሲዎች የሚገኙ አልፎ አልፎም በደላላ ዋጋ ተጨምሮባቸው የሚሸጡ መሆኑን ታካሚዎች ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡

ይህንን ያስቀራል በሚል በተጨማሪም የህክምና ተቋማት የሚሰጧቸውን የተለዩ የህክምና አይነቶች ያካተተ መተግበሪያ የጤና ሚኒስቴር ትናንት አስመርቋል፡፡

መተግበሪያው የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመደገፍና በተለይ ብዙ ችግር የሚታይበትን የመድኃኒት አቅርቦት ስርዓት ለማገዝ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ መተግበሪያውን ካለሙት ባለሙያዎች አንዱ ናቸው አሁን ዲጂታል ጤናን በእንደዚህ አይነት መልኩ መጀመሩ የመድኃኒቶችን ዋጋ እና ቦታውን በቀላሉ ለማወቅ በተጨማሪም መድሃኒቱ ከተገዛ በኋላ ችግር ቢኖርበት ለመመለስም የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

Comments

Avatar