ጋዜጠኞች በነፃነት የመስራት መብታቸው ምን ያህል እየተከበረላቸው ነው?
TRACK

ጋዜጠኞች በነፃነት የመስራት መብታቸው ምን ያህል እየተከበረላቸው ነው?

Avatar

የካቲት 6 2017

ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ የሬዲዮ ቀን እየተከበረ ነው፡፡

ለመሆኑ የሬዲዮ ቀን በምናከብርበት በዚህ ጊዜ የሚዲያው ዋና ተዋናይ የሆነው ጋዜጠኛ በነፃነት የመስራት መብቱ ምን ያህል እየተከበረለት ነው? ዘርፉስ ያለበት ፈተና ምን መሳይ ነው?

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ በሚሆንበት ጊዜ ሚዲያው አብሮ እንዲወድቅ እየተደረገ ነው ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር ተናግሯል፡፡

ይህ እያሳደረ ያለው ጫና ቀላል እንዳልሆነ እና መንግስት ጋዜጠኞች አጥፍተው እንኳን ቢገኙ በህጉ እና በህገ መንግስቱ ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አለበት ሲል ማህበሩ ስረድቷል፡፡

የአለም የሬድዮ ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚዲያው ዋና ተዋናይ የሆነው ጋዜጠኛ ጉዳይን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበሩን ማርታ በቀለ ጠይቃለች፡፡

Comments

Avatar