00:00
ሚያዝያ 7 2017
ማስጠንቀቂያ ሰጥቻቸው የነበሩ ሁሉም የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሁን ላይ መስፈርቱን ስላሟሉ፤ የህጋዊነት ወረቀት ሰጥቻቸዋለሁ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለልጣን ተናገረ፡፡
ባለስልጣኑ ከወራት በፊት ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገሪቱ በስርጭት ላይ ያሉ የሀይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዳሉ ጠቅሶ፤ እነዚህ ተቋማት አስፈጊ የሆኑ መስፈርቶችን አሟልተው ካልተመዘገቡ ህጋዊ ርምጃ እውስዳለሁ በማለት ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
በወቅቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው የሀይማት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፤
1. ኦሲኤን (OCN TV)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima TV)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን (Presence TV) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful TV) ነበሩ፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments
00:00