መጋቢት 23/2018
በኢትዮጵያ ከታክስ የሚሰበሰበው ገቢ በየጊዜው እያደገ ቢሆንም የግብር ስወራውም ቀላል እንዳልሆነ ይነሳል።
ሳይከስሩ ከስረናል ብሎ ማሳወቅ ፤ ትክክለኛ ያልሆኑ የሂሳብ መግለጫዎች ለታክስ አስተዳደር መስሪያ ቤቱ ማቅረብ እና ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት ደረሰኝ አለመቁረጥ ፤ ለግብር ስወራው ማሳያ ሆነው እንደሚቀርቡ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበር ምርመራ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሲሳይ ገዙ ተናግረዋል።
ወጪን አጋኖ ማቅረብ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስን ለመንግስት ገቢ አለማድረግ እንዲሁም ምንም አይነት ግብይት ሳይኖር ፤ ደረሰኞችን ብቻ በመግዛት ሂሳብ ማወራረድም ሌሎች ማሳያዎች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ስራ ከሚሰሩ አንዳንድ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በተገናኘ የሚታየው የታክስ ማጭበርበር ደግሞ በጣም ውስብስብ እንደሆነ አቶ ሢሣይ ነግረውናል።
በአገር ደረጃ በታክስ ማጭበርበር ምክንያት የሚታጣውን ገቢ ለማወቅ ሙከራ መደረጉ አልቀረም የሚሉት አቶ ሲሳይ ፤ ሙከራው ግን በተደረጃ እና ሣይንሳዊ በሆነ መንገድ የተደረገ ጥናት ባለመሆኑ ውጤቱ እንዲህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከበድ ተናግረዋል።
Comments