የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና የተሻለ አሰራር በመፍጠር ማህበረሰቡ በአገልግሎቱ ላይ እምነት ሊኖረው ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ
TRACK

የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና የተሻለ አሰራር በመፍጠር ማህበረሰቡ በአገልግሎቱ ላይ እምነት ሊኖረው ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ

Avatar

ጥር 16 2017

በጤና አገልግሎት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታትና የተሻለ አሰራር በመፍጠር ማህበረሰቡ በአገልግሎቱ ላይ እምነት ሊኖረው ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ፡፡

ለዚህም ያግዛል የተባለ የጤናው ዘርፍ የማህበራዊ ተጠያቂነት ስትራቴጂ ይፋ ተደርጓል፡፡

ስትራቴጂው በጤና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከተቋማት ጀምሮ ባለሙያዎችና አስተዳደር ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችም በመመርመር መፍትሄ ለመስጠት ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ የሚሠራበት ነው ተብሏል።

በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተመለከተ ባለፈው ዓመት 2016 እንኳን በቁጥር የተሻለ አገልግሎት የተሰጠበት ነው ያሉት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ነገር ግን አሁንም የሚቀሩ በርካታ መሻሻል ያለባቸው ስራዎች በመኖራቸው ስትራቴጂው መሰናዳቱን ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ የጤና አገልግሎቶች ላይ የታዩ ለውጦችን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ነገር ግን አሁንም ኢትዮጵያ እየተፈተነችበት ባለው እንደ ግጭትና ወረርሽኞች ምክንያት በጤና ተቋማትና አገልግሎቱ ላይ የደረሱትን ችግሮች ማስተካከል ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Comments

Avatar