መስከረም 24፣2017
በተለይ በአረብ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያዊያን አድራሻቸው በአግባቡ ተመዝግቦ እና መብታቸው ተከብሮ እንዲሰሩ ያግዛል የተባለለት ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነት የተደረገውም በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን እና በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ኤጀንሲ አሰሪዎች ፌዴሬሽን በኩል ነው።
ስምምነቱም ኢትዮጵያዊያን ወደ ውጭ ሀገራት ለመሄድ ህገ-ወጥ የውጭ ሀገራት ጉዞን ለማስቀረትና በህጋዊ መንገድ የሚሄዱ ዜጎችን መረጃ ለማወቅ የሚያግዝ፣ መብት እና ደህንነታቸውንም የሚያስጠበቅ ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአሰሪዎቻቸው የሚደርስባቸው እንግልት እና እስራት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑም ተነግሯል።
Comments