TRACK
ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እየቀረበ ካለው መድሃኒት ከ40 በመቶ በላዩ በሃገር ቤት የተመረተ መሆኑ ተነገረ፡፡
ጥር 27/2018
ለሀገር ውስጥ ፍጆታ እየቀረበ ካለው መድሃኒት ከ40 በመቶ በላዩ በሃገር ቤት የተመረተ መሆኑ ተነገረ፡፡
በ5 ዓመታት ጊዜ ውስጥም የፍጆታውን ከ1/3ኛ ወይም ከ60 በመቶ በላዩን መድሃኒት በሃገር ቤት ማምረት እንደሚቻልም ከጤና ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡
በኢትዮጵያ ለህክምና ግልጋሎት የሚውሉ መድሃኒቶችንና የህክምና ግብዓቶችን ከውጭ በማስገባት የሃገር ውስጡ ፍላጎት እንደሚሸፈን ይታወቃል፡፡
ለረጅም ዓመታት የሃገር ውስጥ የመድሃኒት አምራቾች ድርሻ ከ8 እስከ 10 በመቶ ሳይበልጥ እንደቆየ በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ ህክምና የመድሃኒቶችና ግብዓቶች አቅርቦት አማካሪ የሆኑት አቶ መሃመድ አማን ጀማል ነግረውናል፡፡
የመንግስቱን ጨምሮ በሃገር ውስጥ ያሉ 12 የግል የህክምና መሳሪያና መድኃኒት አምራች ፋብሪካዎች የኢትዮጵያን 40 በመቶ የመድሃኒት ፍላጎት እየሸፈኑ ነው፤ ምርቶቻቸውን እንዲያቀርቡም የተለየ የጨረታ እድል ተከፍቶላቸዋል ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ አምራቾቹ እስከ 7 ዓመት የሚደርስ የገበያ ዋስትና እንዲያገኙና ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ማበረታቻዎች እንዲመቻቹላቸው በመደረጉ በተሻለ መንገድ እያመረቱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
Comments