የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተጀመሩ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለምን ማጠናቀቅ እንደተሳነው ተጠየቀ
TRACK

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተጀመሩ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ ፕሮጀክቶችን ለምን ማጠናቀቅ እንደተሳነው ተጠየቀ

Avatar

ታህሣስ 1፣2017

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከተጀመሩ ከ10 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለምን ማጠናቀቅ እንደተሳነው በፓርላማ አባላት ተጠየቀ፡፡

ባለው ባየ (ዶ/ር) የተባሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ የሚገኘው የረብ ግድብ ከተጀመረ ከ15 ዓመት በላይ እንደሆነው አስታውሰው መቼ አንደሚጠናቀቅ ጠይቀዋል፡፡

የምክር ቤት አባሉ ፕሮጀክቱ ካለመጠናቀቁም በላይ የግንባታው አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለተለያዩ አካላት ብናሳውቅም ችግሩን የሚፈታልን አካል ማግኝት አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መሬታቸውን ለልማቱ የለቀቁ አርሶ አደሮችም ፕሮጀክቱን እንደ እርግማን ነው እየወሰዱት ያሉት ሲሉ ዶ/ር ባለው ባየ አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ ፕሮጀክቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጥሯል ያሉት የምክር ቤት አባሉ ችግሩ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የረብ የመስኖ ፕሮጀክት 45 በመቶ ተሰርቶ አሁን ላይ ግንባታው በፀጥታ ምክኒያት ቆሟል ብለዋል፡፡

ሌላው ጥያቄ የኦሞ ኩራዝ መስኖ ፕሮጀክትን የተመለከተ ነው ጠያቂዋም መሰረት ማዲሎ የተባሉ የምክር ቤት አባል ናቸው፡፡
ጠያቂዋ የኦሞ ኩራዝ የመስኖ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ እየተባለ በተከታታይ በጀት በምክር ቤቱ ጸድቋል ይሁንና አሁንም በተባለው ልክ ፕሮጀክቱ እየተሰራ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Comments

Avatar