የትምህርት ሚኒስትሩ ‘’አጥፊ’’ ሲሉ የጠሩትን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለማስቀረት የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው አሉ
TRACK

የትምህርት ሚኒስትሩ ‘’አጥፊ’’ ሲሉ የጠሩትን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለማስቀረት የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው አሉ

Avatar

የካቲት 25፣2016

የትምህርት ሚኒስትሩ ‘’አጥፊ’’ ሲሉ የጠሩትን የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ለማስቀረት የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው አሉ፡፡

ኢትዮጵያ ልጆቿ በሰላም ወጥተዉ በሰላም የሚገቡባት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ ጥያቄዎች የሚመለሱባት ሀገር እንድትሆን የምሁራን ድርሻ ከፍተኛ ነው ሲሉ ትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ለበርካታ ዘመናት በድህነት በእርስ በእርስ ጦርነት በርሃብ እና በፖለቲካ አለመረጋጋት ስትታመስ መቆየቷን የተናገሩት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ አሁንም ከዚህ አዙሪት ውስጥ መውጣት አንዳልቻለች አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ባለፈው አርባ በዓድዋ ሙዝየም በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተሰናዳ መድረክ ላይ ነው፡፡

‘’ይህንን ያልተጠናቀቀ የሀገረ መንግስት ግንባታ በጥንቃቄ፣ በብልሃት፣ በእዉቀት እና በመተባበር ማጠናቀቅ ያለብን አስቸኳይ የቤት ስራ ነው፤ ይሁን ለማጠናቀቅ በምናደርገው የጋራ ጉዞ ደግሞ ምሁራን ድረሻቸው ከፍተኛ ነው’’ ሲሉም ተሰምተዋል፡፡

‘’ምሁራን ዘላቂ ሰላም እና በሀገሪቱ ቅቡልነት ላለው ሀገረ መንግስት ግንባታ ቁልፍ የሆኑ እንዲሁም በምርምር የታገዙ መፍትሄዎችን በማፍለቅ፤ ሀገሪቱ ከገባችበት ምስቅለቅል እንድትወጣ ዜጎቿ የተረጋጋች ሀገር እንድትኖራቸዉ የማይተካ ድርሻ አላቸዉ’’ ብለዋል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የሀይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ #የንፁሀን_ሞት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar