ነሐሴ 8፣2016
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ 16 ሰዎች በዚህ ዓመት በዝሆኖች ተገደሉ፡፡
ከዚህ በፊት ለባለሀብቶች ተሰጥቶ የነበረው የመጠለያው ክፍል መመለሱን ሰምተናል፡፡
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ፓርክ አካባቢ በዝሆኖች እና በሰዎች መካከል በነበሩ ግጭቶች ምክንያት 16 ሰዎች እና 7 ዝሆኖች ተገድለዋል ተባለ፡፡
አሁን ያለው ህገ ወጥ ሰፋሪ ቁጥር እጅግ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ በሰዎችና በዝሆኖች ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ተብሏል፡፡
የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባንኪቡ ደሞ ለሸገር እንዳሉት መጠለያው አካባቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጉልበት የመጠለያው ክልል እየተጣሰ የሚሰፍር ሰዉ እየበዛ መጥቷል፡፡
Comments