ህዳር 26፣2017
እናቶች በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥማቸው የፎሊክ አሲድ እጥረት ምክንያት የሚወልዷቸው ህፃናት የነርቭ ዘንግ ክፍተት እና የጭንቅላት ላይ ውሃ ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡
ይህን በሚመለከት ሸገር ሬዲዮ ባለሙያ አነጋግሯል፡፡
ባለሙያው ነቢያት ተስፋዬ(ዶ/ር) ይባላሉ፤ በሞያቸው ጠቅላላ ሐኪም ሲሆኑ የህብረተስ ጤና ስፔሻሊስትም ናቸው፡፡
ዶ/ር ነቢያት ስለፎሊክ አሲድ እጥረት ለማውራት በሙያ የታገዙ ብቻ ሳይሆኑ በተፈጥሯቸው የችግሩ ገፈት ቀማሽ በመሆን ልዩ ልዩ ቀዶ ጥገናዎች በአካላቸው ላይ አድርገዋል፡፡
ዛሬ ላይ በአካላቸው ላይ የደረሰው ችግር በሌሎች ህፃናት እንዳይደርስ በተለያዩ በህክምና ተቋማት ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments