TRACK
ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀን ተተምኖ የሚመደበው ሂሳብ ማሻሻያ ከ2017 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች እያጠናቀቅሁኝ ነው አለ
00:00
ሐምሌ 13፣ 2016
ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቀን ተተምኖ የሚመደበው ሂሳብ ማሻሻያ ከ2017 ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራዎች እያጠናቀቅሁኝ ነው አለ፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማር አንድ ተማሪ በቀን ለምግብ የሚታሰብለት ዋጋ 22 ብር ነው፡፡
በዚህ ዋጋ ቁርስ፣ ምሳውና እራቱን መመገብ ይቻል ተብሎ ተተምኖለታል፡፡
አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህ 22 ብር አንዳንድ አካባቢዎች የአንድ ሲኒ ሻይን ሂሳብን እንኳን መሸፈን አይችልም፡፡
በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጨምሮ ዋጋ ማስተካከያ ሊደረግ ይገባል፡፡
Comments
00:00