TRACK
ከተገልጋዮች እጅ መንሻ ተቀብለዋል ያላቸው 88 ሰራተኞቹ ላይ ከስራ እስከ ማሰናበት የደረሰ እርምጃ መውሰዱን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ
00:00
ጳጉሜ 1፣2016
ከተገልጋዮች እጅ መንሻ ተቀብለዋል ያላቸው 88 ሰራተኞቹ ላይ ከስራ እስከ ማሰናበት የደረሰ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡
በየቦታው የኤሌክትሪክ መስመሮች ብልሽት ሲኖር ኑ እና ስሩልን የሚሉ ጥቄዎች ሲቀርቡ ለመስራት ዳተኝነት አለ፤ መጥተው ለመስራትም እጅ መንሻ እንጠየቃለን የሚል ቅሬታ በተገልጋዮች በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡
አገልግሎት መስሪያ ቤቱም እውነት ነው እንዲህ ዓይነት ጥቆማዎች ይደርሱናል፣ የሚበዙት እኛ ጋር ባይደርሱም በዓመት ውስጥ 146 መሰል ጥቆማዎች ደርሰውናል፤ ይህንንም አጣርተን በ88 ሰራተኞች ላይ ከፅህፍ ማስጠንቀቂያ ከስራ እስከ ማሰናበት የደረሰ እርምጃ በስደናል ያሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተሩ አቶ መላኩ ታዬ ናቸው፡፡
Comments
00:00