ከ 400 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ድርጅቶች የሚሳተፉበት የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከ 1 ሳምንት በኋላ በኢግዚቢሽን ማዕከል ሊከፈት ነው
TRACK

ከ 400 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ድርጅቶች የሚሳተፉበት የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከ 1 ሳምንት በኋላ በኢግዚቢሽን ማዕከል ሊከፈት ነው

Avatar

ነሐሴ 10፣2016

ከ 400 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ድርጅቶች የሚሳተፉበት የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከ 1 ሳምንት በኋላ በኢግዚቢሽን ማዕከል ሊከፈት ነው፡፡

ኢግዚቢሽኑም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ይመለከቱታል ተብሎ ተገምቷል፡፡

አዲስ ነገር በአዲስ አበባ ዓመት ሲቢኢ ብር ኤክስፖ የፊታችን ነሃሴ 15 በኤግዚቢሽን ማዕከል ይከፈታል ተባለ፡፡

ስያሜው ሲቢኢ ብር የተባለው ይህ ኤክስፖ ታሚሶል ኮሚኒኬሽን እና ሊየን ቢዝነስ ግሩፕ ከአሴንቲክ ሶሉሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

ኤክስፖ ከነሃሴ 15 እስከ ጷጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ21 ቀናት የሚከናወን መሆኑን ሰምተናል፡፡

ተገበያዮች ወደ ኤክስፖ ሲመጡ ከ10 በላይ መንደሮች በየዘርፋቸው እንደተዘጋጀና የፋይናንስ መንደር ፣ የመዝናኛ መንደር፣ የቴክኖሎጂ ፣ የባህል፣ የገበታ ፣ እንዲሁም የእውቀት መንደር ተብሎ እንደተከፋፈለ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ..

ማርታ በለቀ

Comments

Avatar