በኢትዮጵያ በየዓመቱ 270 ሚሊዮን ኮንዶም የሚያስፈልግ ቢሆንም ወደ ሀገር እየገባ ያለው  ከ90 ሚሊዮን ያልበለጠ መሆኑ ተነገረ
TRACK

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 270 ሚሊዮን ኮንዶም የሚያስፈልግ ቢሆንም ወደ ሀገር እየገባ ያለው ከ90 ሚሊዮን ያልበለጠ መሆኑ ተነገረ

00:00

ህዳር 24፣2017

በኢትዮጵያ በየዓመቱ 270 ሚሊዮን ኮንዶም የሚያስፈልግ ቢሆንም ወደ ሀገር ቤት እየገባ ያለው የኮንዶም መጠን ከ90 ሚሊዮን ያልበለጠ መሆኑ ተነገረ፡፡

ስለዚህም በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል የ180 ሚሊዮን ያህል ጉድለት እንዳለ ያሳያል፡፡

የኤች አይቪ አድስ ቫይረስ (HIV AIDS) እና የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል በሚል ጥቅም ላይ የሚውለው ኮንዶም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጥረት እንዳለ ሲነገር ይደመጣል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ በመስራት ላይ የሚገኘውና የኮንዶም ምርትን ወደ ሀገር ቤት እያስገባ በነፃ የሚያከፋፍለውን ኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን (AIDS HEALTH CARE FOUNDATION) የተባለውን ግብረ ሰናይ ድርጅት ጠይቀናል፡፡

አቶ ቶሎሳ ኦላና በፋውንዴሽኑ የኤችአይቪ መከላከል፣ ምርመራና ተያያዥ ስራዎችን የሚሰሩ የስራ ሃላፊ ናቸው፣ እርሳቸው እንደሚሉት ኢትዮጵያ በኮንዶም አቅርቦት የሚያስፈልጋት 270 ሚሊዮን ሆኖ እያለ መንግስትን ጨምሮ ድርጅታቸው እና ሌላውም ድርጅት ወደ ሀገር ቤት የሚስገባው ተዳምሮ በዓመት ከ90 ሚሊዮን አይበልጥም ብለዋል፡፡

Comments

00:00