00:00
ታህሳስ 22፣2017
በኢትዮዽያ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በተመለከተ ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ ሥነ-ምህዳር እና በሰዎች ደኅንነትና ጤና ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ ተነግሯል።
ይህንን በተመለከተም ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት
ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበጃል የተባለ ረቂቅ ሰነድ ተሰናድቷል።
ውጤታማ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አጓጓዝ፣ አከመቻቸት፣ መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት እንዴት ይዘርጋ የሚለው እረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ አምራቾችን ስጋት ላይ ጥሏል።
Comments
00:00