የ27 ሀገራት ስብስብ የሆነው የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ምርጫ ከቀናት በፊት ተካሂዷል።
በዚህም ምርጫ ‘’ቀኝ ዘመም’’ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድል እንደቀናቸው በሰፊው ተነግሯል።
የህብረቱ የፓርላማ አባላት በአባል አገራት በሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወይም በግል ተወዳድረው ይመረጣሉ።
በአውሮፓ ደረጃ ራሳቸውን በፖለቲካ ፓርቲ አደራጅተው እየተወዳደሩ መቀመጫ የሚይዙም አሉ።
የክርስትያን ዴሞክራቶች ፓርቲ* ስብስብ የሆነው እና በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል (EPP) በሚል የሚታወቀው ፓርቲ አንዱ ነው።
Comments