ግንቦት 13 2017
በብራስልስ ቤልጂየም በሚጀመረው እና ለሁለት ቀናት በሚዘልቀው 3ተኛው የአፍሪካ እና የአውሮፓ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመገኘት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ብራስል መግባታቸው ተሰማ፡፡
በጉባኤው ላይ ለመገኘት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት #IGAD ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ ትላንትና ብራስልስ መድረሳቸውን የኢጋድ ፅ/ቤት ተናግሯል፡፡
በአፍሪካ እና በአውሮፓ ህብረት መሀከል ልዩ ልዩ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ከተጀመረ 25 ዓመታትን ማስቆጠሩ የተነገረ ሲሆን በተለይም በንግድ ፣ በልማት እርዳታ፣ በቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት ቀዳሚ መሆኑ ይነገራል፡፡
በአጠቃላይ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረገው ሶስተኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሀገራቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
በ2022 እ.ኤ.አ የአውሮፓ ሀገራት የቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት #FDI በሚመለከት ከ309 ቢሊዮን ዩሮ በላይ በአፍሪካ መዘዋወሩ ይነገራል፡፡
ከአጠቃላይ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ከሚደረገው የአውሮፓ የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎንም ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጋር የሚገኙ ሌሎች ትብብሮችም በስብሰባው ላይ ይነሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አጀንዳው ይናገራል፡፡
Comments