በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጎዱ  የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናት አሳየ
TRACK

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጎዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናት አሳየ

Avatar

ሰኔ 6፣ 2016

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጎዱ እና በተመሳሳይ ተፈጥሮዊ አደጋ የሚያጋጥማቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናት አሳየ።

ጥናቱን ላለፉት 30 ዓመታት የነበረውንና አሁን ላይ ያለውን የከተማዋ የአየር ሁኔታን የሚያሳይ መሆኑንም ሰምተናል።

በከተማዋ የጎርፍ መጨመር፣ የመሬት መንሸራተት፣ የሙቀት መጨመር፣ የዝናብ መጠን መቀነስና የድርቅ ሁኔታ መባባስ የጥናቱ ግኝት መሆናቸው ተነግሯል።

አሁን ያለው የዝናብ መጠን ካለፉት ዓመታት አንፃር ከ20 እስከ 50 ፐርሰንት መቀነስ እንደታየበትም በጥናቱ ተመላክቷል።

ሌላኛው በጥናቱ ከተዳሰሱት ጉዳዮች ውስጥ የሙቀት መጠን ሁኔታ አንዱ ነው በጥናቱም በከተማው የሙቀት መጠን መጨመሩ ተነግሯል። አሁን ያለው ሙቀት መጠንም በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ትልቅ አደጋ ይዞ ይመጣልም ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 2050 ድረስ የሙቀት መጠኑ ከአንድ እስከ ሁለት ድግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊጨምር እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ ተብሏል።

ይህም ማለት በአለም አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው የሙቀት አማካኝ መጠን ከአንድ ነጥብ አምስት ድግሪ ሴንቲ ግሬድ ከጨመረ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደሚጥል ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…

ፍቅሩ አምባቸው

Comments

Avatar