ህዳር 3፣ 2017
የተሳከረውን የሪል ስቴት ገበያ መፍትሄ ያቀርባል የተባለው በኦዲተሮችና በሂሳብ ባለሙያዎች ሀሳብ ያዋጣል የተባለ እንዲሁም በአጠቃላይ በካፒታል ገበያ እና ኢንቨስትመንት እድል ዙሪያ የተሻለውን ያመጣል የሚል ሰፊ አለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ልታስተናግድ ነው፡፡
ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ የብሔራዊ ባንክን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርን እንዲሁም ከውጪ የአለም ባንክን የአፍሪካ ልማት ባንክና ዩኤንዲፒ(UNDP)ን እንደሚያሳትፍ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል፡፡
በዚህ ጉባኤ የካፒታል ገበያው ቁጥጥር እንዲበረታ ዘላቂ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር ይመከርበታል ተብሏል።
አለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮው ምንድነው? ፊንቴክና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ከገበያው ጋር እንዴት ይጣጣማል በሚለው ጉዳይ ሀሳብ ይዋጣበታል ተብሏል።
Comments