የአዲስ አበባ አከራይ እና ተከራዮች በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን አዋጅ መሰረት በማድረግ ህጋዊ ውል እየገቡ ነው ተባለ
TRACK

የአዲስ አበባ አከራይ እና ተከራዮች በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን አዋጅ መሰረት በማድረግ ህጋዊ ውል እየገቡ ነው ተባለ

Avatar

ሰኔ 6፣ 2016

የአዲስ አበባ አከራይ እና ተከራዮች በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን አዋጅ መሰረት በማድረግ ህጋዊ ውል እየገቡ ነው ተባለ፡፡

መንግስት በቅርቡ ያወጣው የአከራይ እና ተከራይ አዋጅ አከራይንም ተከራይንም ለህግ ተገዢ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

አዋጁ መተግበር ከተጀመረ 6 ቀኑን ይዟል፡፡

አብዛኛው ተከራይ አንድ ቦታ ተረጋግቶ መኖር ተስኖታል የተባለ ሲሆን ይህ አዋጅ ወይንም መመሪያ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ቢያንስ 2 አመት አንድ ቦታ ላይ መኖር ያስችለዋልም ተብሏል፡፡

አንድ አንድ ተከራዮችም ከተከራዩ በኋላ አልወጣም በማለት ጉዳዮ እስከ ፍርድ ቤት እንደሚደርስም ሰምተናል፡፡

ይህ አዋጅ ይህንን እንደሚያስተካክልም ተነግሮዋል፡፡

ተከራዩ የሚፈጥረው ችግር እና በቤቱ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በተጨባጭ ከተረጋገጠ ሁለት አመት እዛ ቤት ውስጥ ሊቆዩ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ተናግሯል፡፡

አሁን ላይ መንግስት በዚህ ብር አከራዩ የሚል ድንጋጌ እንዳላደረገና ወደፊት ግን በአመት አንድ ጊዜ ሰኔ አንድ ላይ የገበያ ጥናት ካደረገ በኋላ የኑሮ ውድነቱን፡ ጫናውን ታሳቢ በማድረግ ለሁሉም በእኩል ወጥ የሆነ በፐርሰንት እንደሚያስቀምጥ ሰምተናል፡፡

ማርታ በቀለ

Comments

Avatar