በጤና እና በግብርና ሚኒስቴር ስር ያሉ 22 ተጠሪ ተቋማት ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚሰሩት ስራ አጥጋቢ አይደለም በሚል ተተቹ፡፡
TRACK

በጤና እና በግብርና ሚኒስቴር ስር ያሉ 22 ተጠሪ ተቋማት ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚሰሩት ስራ አጥጋቢ አይደለም በሚል ተተቹ፡፡

00:00

ታህሳስ 24/2018

በጤና እና በግብርና ሚኒስቴር ስር ያሉ 22 ተጠሪ ተቋማት ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንን እና ሌሎች ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚሰሩት ስራ አጥጋቢ አይደለም በሚል ተተቹ፡፡

ትችቱን ያቀረበው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በስርዓተ ጾታና በማህበራዊ አሳታፊነት ወይም አካቶ ዙርያ በ22 የጤና ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ላይ ያደረገውን የምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል።

ተቋማቱ የተመዘኑትም የሴቶችን፣ የሕፃናትን ፣ የወጣቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን፣ የአረጋዊያንን እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳዮች በስራዎቻቸው ምን ያህል አሳትፈዋል? ምን ያህልስ ተጠቃሚነታቸውን አረጋግጠዋል? በሚል ነው።

ምዘና ከተደረገባቸው ተቋማት ዉስጥ አብዛኞቹ ዝቅተኛ አፈፃፀም እንዳስመዘገቡም ተነግሯል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እርጎጌ ተስፋዬ ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በስራዎቻቸው በበቂ ሁኔታ ያላሳተፉ ተቋማት ብዙ ናቸው ብለዋል።

ይህም የሆነበት የአመራር ቁርጠኝነት ማነስ፣ የተጠያቂነት ስርዓት አለመስፈን፣ የተቋማት የጋራ ትብብር አለመኖርና በመሰል ችግሮች እንደሆነም ነግረውናል።

Comments

00:00