አዲሱ የካላዛር ህክምና ወደ ምእራፍ 2 የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ ተሰማ
TRACK

አዲሱ የካላዛር ህክምና ወደ ምእራፍ 2 የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ ተሰማ

00:00

ሚያዝያ 15፣2016

አዲሱ የካላዛር ህክምና ወደ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡

ካላዛር ከወባ ቀጥሎ በዓለም ላይ በጥገኛ ተህዋሲያን የሚተላለፍ ገዳዩ በሽታ ነው፡፡

በሽታው ትኩሳት፣ የክብደት መቀነስ፣ ከልክ ያለፈ የጣፊያና የጉበት እድገት ያስከትላል፣ በጊዜው ካልታከመም ለሞት ሊዳርግም ይችላል፡፡

ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩን ተናግሯል፡፡

ወደ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ የተነገረው መድሃኒቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ፣ አስተማማኝ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ለህሙማን ምቹ የሆነ በአፍ የሚወሰድ ነው ተብሏል፡፡

የካላዛር መድሃኒት ለማስገኘት የሚያካሂዱት ምርምር አዲሱ የካላዛር ህክምና በእጅጉ ትኩረት የተነፈገውንና ለማከምም አስቸጋሪ የሆነውን የካላዛር በሽታ ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ተብሎለታል፡፡

Comments

00:00