TRACK
ባለፉት 18 ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ሞያተኞች እና ሰራተኞች ሰልጥነው በአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ መሰመራታቸው ተነገረ፡፡
ግንቦት 22 2017
ባለፉት 18 ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ሞያተኞች እና ሰራተኞች ሰልጥነው በአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ መሰመራታቸው ተነገረ፡፡
ለዘርፉ ስልጠናዎችን በተለመደው መንገድ መስጠት ብቻ በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ አዳዲስ አሰራሮችን መከተል ግድ ሆኗልም ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያን የአበባ፤ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የሚገዙ ሀገራት እንደ ቅድመ ሁኔታ ከሚያቀርቧቸው ጉዳዮች አንዱ፤ በዘርፉ የሚሰሩ ሰዎች ተገቢውን ስልጠና የተከታተሉ ናቸው ወይ? የሚል ነው።
ይህን ጥያቄያቸውን ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ አበባ ፤ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች እና ላኪዎች ማህበር ከጎርጎርሳውያኑ 2007 ጀምሮ ስልጠና ሲሰጥ እንደቆየ ሠምተናል።
ማህበሩ ስልጠናውን ሲሰጥ የቆየው ለዚሁ ብሎ ባቋቋመው የስልጠና ማዕከል እንደሆነ የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ተናግረዋል።
Comments