ጥር 25/2018
በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቆይተዋል፡፡
በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ለተከታታይ 3 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው ላይ አልነበሩም፡፡
በተለይ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች በነበሩ አሁንም ድረስ በቀጠሉ የሰላም እጦቶች ተማሪዎች ቀያቸውን ለቀው ወጥተዋል፣ ትምህርት ቤቶች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ልጆች ከእስክርቢቶ እና ደብተር እርቀው ሰንብተዋል፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተማሪዎችም ከትምህርት ቤት በራፍ ሳይደርሱ ከርመዋል፡፡
Comments