ሰኔ 6 2017
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዝግ አድርጎት የነበረውን፤ የኩዌት የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ተጀመረ፡፡
ከዚህ ቀደም አስፈላጊ የሚባለውን ስልጠና አጠናቅቀውና በግላቸውም ቢሆን የስራ ስምሪቱን ያገኙ ወጣቶች መሄድ አልቻልንም ብለው እንደነበር ይታወሳል፡፡
በወቅቱ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኩዌት ጋር ምንም ዓይነት የስራ ውል የለኝም ስለዚህ የሰለጠነውን የሰው ኃይል አልክም በማለት መልስ ሰጥቶ ነበር፡፡
አሁን ኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ ያሰለጠነቻቸውንም ይሁን አግባብነት ያለው መረጃ በማቅረብ በግላቸው የሚመጡ ሰዎችን ለመላክ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ሰምተናል፡፡
ሁለቱ ሀገሮች የአለም አቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን፤ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሃምሳሉ ባሻ ነግረውናል፡፡
Comments