ግንቦት 19፣2016
ምጣኔ ሐብት
ኢትዮጵያ የሀገር ቤቱም የውጭውም ተደምሮ ያለባት ብድር ወይም እዳ 65.7 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡
ሀገሪቱ ለዚህ ብድር በዚህ ዓመት እስካሁን ድረስ 1.9 ቢሊዮን ዶላር እዳ ለመክፈል ብታቅድም መክፈል የቻለችው ግን 1.1 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከግማሽ ጥቂት ያለፈውን ነው፡፡
ሀገሪቱ ያለባት እዳ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቱ ጋር ሲነፃፀር ችግር ውስጥ የገባ ነው ሊባል የሚችለው አይደለም ሲል መንግስት ያስረዳል፡፡
አሁን እየተገኘ ያለው ወይም ቃል እየተባ ያለው ብድርም ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ተብሏል፡፡
ስለ ብድር ጫናው እና ተያያዥ ጉዳዮች በምጣኔ ሀብት ዝግጅታችን ተመልክተነዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
#Ethiopia #ShegerWerewoch #የውጭ_እዳ #ብድር #Loan #ምጣኔ_ሐብት
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments