00:00
የካቲት 26 2017
የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ከትራንስፖርት ባለፈ በአለም ግዙፍ ኢኮኖሚ በሚገላበጥበት የዕቃ ገቢና ወጭ ማስተላለፍ የመርከብ ክሊራንስ የጉምሩክ ማለፍያ ሰነድ አጠናቆ ከጅቡቲ ወይም ከመነሻ ሀገር እቃ ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ።
ይህ በመሆኑ አስመጭ ላኪዎች በውጭ ምንዛሪ የሚከፍሉት ቅጣትና የመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከገቢና ወጭ ንግድ መሀል ያለውን መዝረክረክ በብርቱ ያስቀራል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ገቢና ወጭ ንግድ ያቀላጥፋል የተባለለት ጥልፍልፍ አሰራሮችንም ያስቀራል በሚል ተስፋ የተደረገበት ስርአት ዘርግቶ በዚያው መንገድ መጓዝ መጀመሩን የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ተናግሯል።
በኢትዮጵያ በግዙፍ ኢኮኖሚ በወጭና ንግድ ገቢ ንግድ ማዕዘን ከትራንስፖርት ባለፈ ተመልካች የነበረው
የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የፍሬይትና የመልቲ ሞዳል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ይህንኑ አገልግሎት እንዲሰጥ ፈቃድ ሰጥቷል ተብሏል።
Comments
00:00