አዋጭ የተሰኘው የብደርና ቁጠባ ተቋም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል፡፡
TRACK

አዋጭ የተሰኘው የብደርና ቁጠባ ተቋም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል፡፡

00:00

ታህሳስ 23፣2017

አዋጭ የተሰኘው የብደርና ቁጠባ ተቋም በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል፡፡

ከተቋሙ ብድር ወስደው የተለያየ ምርት እያመረቱ ያሉ ከ70 በላይ ለሆኑ አባላቱ በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ሾላ የገበያ ማዕከል ውስጥ በራሱ የግል ይዞታ ባዛር አሰናድቶዋል፡፡

አዋጭ ቁጠባን ከአባላቱ በማሰባሰብ ለ42,000 አባላቱ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጥቶ እያንቀሳቀሰ እንደሆነ እየተናገሩት የህብረት ስራ ማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ሸለመ ናቸው፡፡

ይህ ባዛር አዋጭ ለአባላቱ ብድር መስጠት ብቻ ሳይሆን የተሰጠው ብድር ከምን እንደደረሰ ማሳያ ነው ያሉት ደግሞ የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ዋና ስብሰባ አቶ መስፍን ገብረስላሴ ናቸው፡፡

ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 2017 ዓ.ም በሚቆየው የገና ባዛር ተሳታፊ አባላት የራሳቸው ምርት እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን ይዘው በመቅረብ ለሸማቾች ምቹ ገበያን ይፈጥራሉ ተብሏል፡፡

Comments

00:00