‘’የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ለሸማቹ ብቻ ሳይሆን ለመንግስትና ለአልሚዎችም አስፈላጊ ነው’’ የፋይናንስ ባለሙያ አቶ መርዕድ ፍቀርዮሃንስ
TRACK

‘’የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ለሸማቹ ብቻ ሳይሆን ለመንግስትና ለአልሚዎችም አስፈላጊ ነው’’ የፋይናንስ ባለሙያ አቶ መርዕድ ፍቀርዮሃንስ

Avatar

የካቲት 28 2017

ባለፈው ሳምንት ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ባንኮች አንድ ዶላር በ135.6 ብር መግዛታቸው ይታወሳል፡፡

ይህም የብርን የመግዛት አቅም ያዳከመ፣ ዶላር ደግሞ የበለጠ አቅም እንዲያገኝ ያደረገ ነው፡፡

የብር የመግዛት አቅም በህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ከማዳከም፣ ከባንኮች የተቀማጭ ገንዘብ መመናመንም ባሻገር በመንግስትም ላይ ተፅዕኖው ከፍ ያለ መሆኑን የፋይናንስ እና እንቨስትመንት ባለሙያ አቶ መርዕድ ፍቀርዮሃንስ ይናገራሉ፡፡

መንግስት እዳውን የሚከፍለው፣ እንደ ነዳጅ ያሉ የገቢ ምርቶችን የሚሸምተው በውጭ ምንዛሪ በመሆኑ እንዲህ ያለውን አካሄድ ሊያጤነው ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ግብይት እና የተረጋጋ የገበያ ሥርዓት ለሸማቹ ብቻ ሳይሆን ለመንግስት እና ለአልሚዎችም አስፈላጊ መሆኑን ነግረውናል፡፡

አሁን ያለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተገማች እና ግልጽ መሆን አልቻለም ያሉት ባለሞያው ይህንንም ማስተካከል እና ወጥ ማድረግ ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r

Comments

Avatar