00:00
ህዳር 12፣2017
ህፃናት ወደ ከተማ ሲመጡ ህገ-ወጥ ደላሎች የጉልበት ብዝበዛ እንደሚያሰማሯቸው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ።
ፍልሰቱም በስፋት ከሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች ቀዳሚው ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያ መሆኑ ተነግሯል።
የሀገር ውስጥ ፍልሰት የሚጨምርበትም የሚቀንስበትም ወቅት አለው የሚለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሀገር አሁን ላይ እያጋጠሙን ባሉ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መጨመር የፍልሰቱ መጠን ከፍ እንዲል አድርጎታል ብሏል።
ህገ-ወጥ ደላሎች በብዛት የሚገኙት አዲስ አበባ በመሆኑ ለጉልበት ብዝበዛም ሆነ ለሌላ ሌላውም ለህፃናት ፍለሰት ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ድሬዳዋ፣ አዳማ እና ሐዋሳ በቅደም ተከተላቸው ከፍተኛ ፍልሰት ከሚያስተናዱ ከተሞች መካከል ናቸው ተብሏል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments
00:00