መጋቢት 30 2017
በማይናማር በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ታጉረው ከወር በላይ እንደቆዩ የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ተታለው ወደ ማይናማር የሄዱና በዛም በማይከፈላቸው ህገ-ወጥ ስራዎች እና በስቃይ ውስጥ እንዲቆዩ የሚናገሩት ኢትዮጵያውያን ከዛ ህይወት ወጥተው ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ ቢሆንም መንግስት ቶሎ ሊደርስልን አልቻለም ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በዛው በማይናማር በዲኬቤና ሌላም ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው ያሉት ኢትዮጵያውያን በቁጥር ከ700 በላይ ነን ብለዋል፡፡
በቦታው ውሃ እና ምግብ በአግባቡ እንደማይቀርብላቸው እና ለበሽታም እየተጋለጡ መሆኑን ነግረውናል፡፡
መንግስት ይድረስን የሚል ጥሪ ያቀረቡት ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም ህገ-ወጥ ስራ ያሰሩን ነበር እየደበደቡም እያሰቃዩን ነበር ያላቸው ግለሰቦች እየመጡ እንደገና ወደነበርንበት ስቃይ እንድንመለስ የካምፑን ሀላፊዎች እያነጋገሩ በመሆኑ ስጋት ገብቶናል እያሉ ነው፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments