ሐምሌ 24፣2016
ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ማድረጓን ከቀናት በፊት አሳዉቃለች፡፡
ይህ የማክሮ ኢኮኖሚ አንዱ ያሳካልኛል ብላ ሀገሪቱ ያሰበችው ደግሞ በኢትዮጵያ ያለውን የባለ ሁለት ዲጅት የዋጋ ንረት ወደ አንድ ዲጂት ያወርዳል የሚል ነው፡፡
ለዚህም ማሻሽያ ማስፈጸሚያ ይረዳኛል ያለቸውን ብድር ከአለም አቀፍ የገንዝብ ተቋም የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያው አማካይነት እንዲሆን በመወሰኗ አግኝታለች፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ማሻሽያ ያደረገበት የማክሮ ኢኮኖሚ አንዳለው የአገሪቱን የዋጋ ንረት ወደ ነጠላ አሃዝ ያወርደው ይሆን?
በኢትያጵያ ኢኮኖሚ በለሙያዎች ማህበር የጥናት እና የፖሊሲ ትንተና ዳይሬክተር የሆኑት ድግዬ ጎሹ (ዶ/ር) ማሻሽያው የአገሪቱን በለሁለት አሀዝ የዋጋ ንረት ወደ ነጠላ አሃዝ ማውረድ አይችልም ይላሉ፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ያዋጋ ንረቱ ከቀነሰም ሊቀንስ የሚችለው የህዝቡ የመግዛት አቅሙ በመዳከሙ ነው እንጂ ምርት ሞልቶ እና ዋጋው ቀንሶ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
አንዴት አንደሆነም ያብራራሉ።
Comments