በአውሮፓውኑ 2030 ረሃብና ድህነትን ከዓለም ለማጥፋት የተቀመጡ ግቦች እንደማይሳኩ ከመግባባት ላይ መደረሱ እየተነገረ ነው፡፡
TRACK

በአውሮፓውኑ 2030 ረሃብና ድህነትን ከዓለም ለማጥፋት የተቀመጡ ግቦች እንደማይሳኩ ከመግባባት ላይ መደረሱ እየተነገረ ነው፡፡

Avatar

ህዳር 12፣2017

በአውሮፓውኑ 2030 ረሃብና ድህነትን ከዓለም ለማጥፋት የተቀመጡ እንደማይሳኩ ከመግባባት ላይ መደረሱ እየተነገረ ነው፡፡

ዘላቂ የልማት ግቦች በሚል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃገራት እንዲፈፅሟቸው የተቀመጡ ግቦች እንደማይሳኩ በአብዛኛው መግባባት ላይ መደረሱን በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ሃሳባቸውን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምግብና ኒውትሪሽን ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት አሻግሬ ዘውዱ ነግረውናል፡፡

ከዚህ ላይ የተወሰኑ ማሳያዎችን እንጥቀስ በአውሮፓውኑ 2030 ረሃብን ከዓለም ማጥፋት ይቻላል በሚል ቢቀመጥም አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አፋጣኝ ድጋፍ ይፈልጋሉ፤ በአለም ዙሪያም ከ800 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል፡፡

እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (UNDP) የዘንድሮ ዓመት 2017 ሪፖርት መሰረት በአለም ዙሪያ ከ1.1 ቢሊዮን በላይ ሰዎች በድህነት ውስጥ ናቸው፣ ኢትዮጵያም 68 በመቶ የተጠጋ ህዝቧ ድህነት ውስጥ ነው በሪፖርቱ መሰረት፡፡

የሥነ ምግብ ተመራማሪው እንደሚሉት በተመድ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት 5 ዓመታት ብቻ ነው፤ በዚህ አካሄድ ውጥኑ ሊሳካ አይችልም፡፡

ለዚህ የበቃነውም በተለይ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወዲህ ሌሎችም ምክንቶች ተዳምረው ድህነትን ለመቀነስ ለደሃ ሃገራት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ ሃገራት ድጋፋቸውን በማቆማቸው ሂደቱ እንደተደናቀፈ ያነሳሉ፡፡

Comments

Avatar